Wednesday, July 11, 2012


ማን ነህ አንተ የምትደኛኝ?

እንደ እኔ ሰይቸግርህ
ኑሮ ሳያንከራትትህ
በማንናትህ ሳይመጡብህ
ራስህን ሆነህ ኖረህ
እንዳስፈለገህ ተናግረህ
ወጥቶልህ ሃሳብህ
እንደ አሰኘህ
የኔ ሰይገባህ
የምትወቅሰኝ እንዳማረህ
አንተ ማን  ነህ ?
አዎ እኮ አንተ ማን ነህ?

እስት ይታይህ በራሴ ሃገር
በእትብቴ ምድር
በአያቶቼ ማቃብር
ስገፉኝ ስወረዉሩኝ እንደ ተራ ነገር
ኡ ብዬ ብጮህ ልጣራ ስጣጣር
ለምን ይባላል ምን ይምጣ ምን ይፈጠር?